-
-
This article is more than 1 year old

አገራዊ ዕውቅናን መቸር

SBS ለአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች እንደ እዚህች አገር ልማዳዊ ባለቤቶች፣ ዘላቂና ከየብስ፣ባሕር፣አየርና ማኅበረሰብ ጋር ያልተቋረጠ ግንኙነት ዕውቅናን ይቸራል።

Published 3 July 2023 8:01am
Source: SBS
Image: - (Julia Esteve/Getty Images)
በተለምዶ አገራዊ ዕውቅና የሚቸረው እንደ ንግግሮችና ስብሰባዎች ባሉ ሕዝባዊና ግላዊ ኩነቶች ወቅት ማስተዋወቂያና እንኳን ደህና መጣችሁ ከመባሉ በፊት ነው።

ኩነቶች ሲካሔዱ ለአገር ልማዳዊ ባለቤቶች ዕውቅናን የመስጫ መንገድ ነው።

የ SBS ኦዲዮ ፕሮግራሞች የሚጀምሩት በእዚያ ፕሮግራም አገራዊ ዕውቅናን በመቸር ነው።

ይህንንም የምናደርገው የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ከአገር ጋር ላላቸው ትስስሮሽ ዕውቅናን ለመቸር፣ ለቀደምትና አሁነኛ አረጋውያን ከበሬታችንን ለመግለጥ ነው።

እንዲሁም አውስትራሊያ ከቶውንም ሉዓላዊነቷ ያልተደፈረ ስለ መሆኑም ዕውቅናን ለማላበስ ነው።

ለአገራዊ ዕውቅና በተለይ የተፈረጀ የቃላት አጠቃቀም የለም፤ እናም ማንኛውም ሰው ማለት ይችላል።

ወደ አገር እንኳን መጣችሁ የሚነገረው በልማዳዊ ባለቤቶች ወይም በአቦርጂናልና ቶረስ ደሴት ሰዎች ከልማዳዊ ባለቤቶች የጎብኚዎች ወደ አገራቸው መምጣትን ለመቀበል ፈቃድ በተሰጠው ሰው ነው።

የአገራዊ ዕውቅና ምሳሌን አነሆ፤

ለመሬቶች፣ ሰማዮችና የውኃ መስመሮች ልማዳዊ ባለቤቶች ዕውቅናን ልንቸር፤ ለቀደምትና አሁነኛ አረጋውያን ከበሬታችንን ልንገልጥ እንወዳለን። የዓለም አንጋፋና ቀጣይ ለሆነው ባሕል ከበሬታዎቻችንን እንገልጣለን።
LISTEN TO
Acknowledgement of Country in Amharic image

Acknowledgement of Country in Amharic

00:29
የአካባቢ ማዘጋጃ ቤቶች፣ ክፍለ አገራት ወይም ግዛቶችን ድረገጾች በመጎብኘት ወይም ከአካባቢው የአቦርጂናልና ነባር ዜጎች ድርጅቶች ጋር በመገናኘት እርስዎ የሚገኙበት መሬት ልማዳዊ ባለቤቶች እነማን እንደሆኑ ማወቅ ይችላሉ።


Share